የውክልና አገልግሎት

  • ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ከሆነ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሮዎት
    • ኤምባሲው ዘንድ በአካል የሚቀርቡ ከሆነ የውክልና ሰነዱን ኦፊሰሩ ባለበት ፈርመው ማስፈፀም ይኖርበታል
    • ውክልናው በመልዕክት / mail / የሚልኩ ከሆነ ሰነዱን ኖተራይዝ አድርገው አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ይጠበቅበታል፡፡
  • የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት፡-
  • ውክልናውን በአማርኛና በእንግለሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት ስቴት ኦፊስ ቀጥሎ ዋሽንግተን ዲሲ ወደሚገኘው ስቴት ዲፓርትመንት በመላክ አረጋግጦ መቅረብ/መላክ
  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡