Order Wikilina/ውክልና ያሰሩ

NEW
—————-

Pay Now

CHOOSE YOUR ORDERበቅድሚያ ወደ ድረ ገጻችን እንኳን ደህና መጣችሁ። ይህ ድረ ገፅ የተሰራው ከብዙ አመታት ልምድና በደንበኞችን አስተያዬት ላይ በመመርኮዝ  ስለሆነ እባክዎ ጊዜዎን ወስደው የዚህን ድረ ገፅ ዋና አላማ በጥሞና ያንብቡት። ውክልና ቀልድ አይደለም ። በቅድሚያ አንድን ሰው ለወከል ከማጨትዎ በፊት ያ ተወካይ ለምን እና ምን አይነት የውክልና ስልጣን እንደሚሰጡት በጥሞና ያስቡበት። የውክልና ስልጣን መስጠት ሳይሆን የውክልና ስልጣኑን ከተወካዩ ላይ ማውረዱ ወይም መሻሩ በጣም ከባድ ሂደት ነው። ታዲያ እኛ ለደንበኞቻችን  የውክልና ስልጣን  መስጫም ሆነ መሻሪያ ሰነድ ማዘጋጀት ያካበትነው ልምድ  በጣም ብዙ አመታትን የፈጀ  ልምድ ስለሆነ በኛ በኩል የተዘጋጀ የውክልና ማስረጃ ቅመም የሆነ እርስዎን ከብዙ ውጣ ውረድ የሚያድን በጣም የተዋጣለት ፍቱን መድሀኒት ነው።
ስራችን አገር ቤት  የራፖር ፀሀፊወች አይነት ወይም ገና ለገና የአማርኛ ታይፕ ማድረግ ሰለቻሉ ብቻ ከኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይም ከሌላ ሰው አሮጌ ወይም ናሙና የውክልና ስልጣን ገልብጠው የአንዱን ከአንዱ አጋጭተው ሌላ ጣጣ ውስጥ ሰውን የሚከቱ አይነት መናኛ ስራ አይደለም። ስራችን  በአለም አቀፍ የጄኔቫ እና ሄግ ውሎች መሰረት ተመርኩዞ የሚሰራ ስለሆን  ውክልናም ሆነ ሌሎች ሰነዶች በአለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ፍርድ ቤቶች፣ ኢሚግሬሽን ፣ አየር መንገዶች፣ ኢምባሲወች፣ ባንኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ ዩንቨርስቲወች፣  ቀበሌወች፣ ክፍለ ከተሞች፣ ክልሎች፣ አስተዳደሮች፣ ቴሌ ኮሚኒኬሽን፣ የጡረታ መምሪያ፣ የሴቶች ጉዳይ መምሪያ፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመሬት አስተዳደር እና በመሳስሉት ቁልፍ ቦታዎች እንዲሰሩ ሆነው የረቀቁ ሰነዶች ናቸው ::አላማችን  እርስዎ ያለወትን  ጉዳይ  በወቅቱ  እንዲያጠናቅቁ ነው:: ይህ  ማለት  የውክልናውን ሰነድ  የፈለጉበት ዋናው አላማ ግቡን  እንዲመታ ነው።  አንዳንድ  ጊዜ  አንዳንድ  ደንበኞች  ከውቀት ማነስ የተነሳ  ውክልና ማዘጋጀት  የወካይና የተወካ  አድራሻን  ብቻ  ቀይሮ የሌላ ሰው ውክልና ቃል በቃል መገልበጥ ብቻ  ይመስላቸውና  መጠኑ ልቅ የሆነ ወይም ጎዶሎ  የውክልና ስልጣን ሰጠው  የራሳቸውንም  ሆነ የሰውን  ጊዜ፣ሂወት እና ገንዘብ ሲያባክኑ ማየት የተለመደ ነው።ይህንን አገልግት በአለም አቀፍ ደረጃ  ለህዝብ ስናቀርብ  እስከ ዛሬ ለብዙ አመታት ያካበትነው የስራ ልምድ ተጠቃሚዎች በካሊፎርያ  ግዛት ብቻ ነዋሪዎች  ብቻ  ስለነበሩ ይህንን አገልግሎት ለሌሎችም  ብንሰጥ ታላቅ ጥቅም ይኖርዋል  ብለው  ብዙ  ደንበኞቻችን  ስለነገሩን  ነው። ዛሬ ወገኖቻችን/ደንበኞቻችን  በአራቱም የአለም ማእዘናት ተበትነው ሰለሚገኙ  የዚህ አገልግሎት ተጥቃሚ ለማድረግ ይህንን እድል  ስንከፍት  የመጀመሪያው  ስንሆንን ይህንን  አገልግሎት ለመስጠት እድሉን ስናገኝ በጣም  ደስተኞች  ነን ። ተጠንቀቁ። ከልክ ያለፈ ወይም  ውስን ውክልና ሰጥተው  በገንዘብዎ ወይም በንብረትዎ ላይ እንዳይፈርዱት ። ይህን የምንለው እርስዎን ለማስፈራራት ሳይሆን  አስቀድሞ ለማስጠንቀቅ ነው::  የውክልና ስልጣን  ማስረጃ  የሚሞላ ፎርም  አይደለም ። ነገር ግን እንደ እየ ሁኔታው የሚረቅ  ህጋዊ ሰነድ ነው::እኛ  ጋር  ውክልና ለማዘጋጀት  ሲመጡ ወይም በስልክ  ሲደውሉልን መጀመሪያ  ብዙ  ቃለ  መጠይቅ  እናቀርብልወታለን ፣ ከዚያ  እርስዎ በፈለጉት  መሰረት  ያሰቡትን  ተግባር  የሚፈፅም  ቅምም  የሆነ  የውክልና   ማስረጃ ሰነድ እናዘጋጃለን ። ከዚያ   የውክልና ስልጣኑ  ሙሉ  በሙሉ  ህጋዊ እንዲሆን ምን  ምን  እንደሚያስፈልግዎ  ቅደም  ተከተሉን  እናስረዳዎታለን ። አሰራራችን  ወይም  ጠቅላላ  ሂደቱ ትንሽ  እረዘም  ያለ  ነው። ለዚህም በቂ ምክንያት አለን ::  ምክንያታችንም ሲሮጡ  የታጠቁት  ሲሮጡ  ይፈታል  እንዳይሆን  ነው::  ታዲያ  ችኮላ  ጠላታችን  ነው ። ከሁሉ ነገር  ለኛ  የሚያስደስተን  ነገር በስራችን  ጉዳዩን  ያስጨረሰ ደንብኛ ማየት ነው::  ታዲያ እኛ  ባዘጋጀነው የውክልን ስልጣን ማስረጃ ሰነድ ጉዳያቸውን ያስፈፀሙ ደንበኞቻችን በጣም ብዙ ናቸው:: ታላቁ  ማወቅ  ያለብዎት ቁም  ነገር   የእርስዎ   ውክልና ስልጣን ማስረጃ በግምት አይሰራም።  ያ  ማለት ደግሞ የእርስዎን ሰነድ  ልክ እንደ መለማመጃ   አናደርግውም።  ያለን  የስራ ልምድ ከ 15 ዓመታት በላይ ሲሆን በጣም ብዙ  የውክልና ሰነዶችን  ሰለሰራን  ምን  ለምን እንደሚጠቅም  ጠንቅቀን  እናውቃለን ።የኛን  ስራ  በመጠቀም  ደንበኞቻችን  ከፈፀሟቸው ጉዳዮች መካከል ለምሳሌ ደንበኞቻችን፦

 • ልጆቻቸውን ወደ አሜሪካ አስመጥተዋል
 • የውርስ መብት አስክብረዋል
 • ቤትና ንብረት ሽጠዋል / ገዝተዋል
 • የንግድ ድርጅት ሽጠዋል / ገዝተዋል
 • ሆስፒታል፣ክሊኒክሰርተዋል
 • ቤት የንግድ ድርጅት፣ መኪና ማሽን አከራይተዋል
 • የጉዲ ፈቻ ውል ፈፅመዋል
 • የጋብቻ፣የፍቺ እና የልደት የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል
 • ኮንዶ፣ መሬት፣መኪና ተረክበዋል
 • ከባንክ ገንዘብም ማስወጣትም ሆነ ማስገባት ችለዋል
 • ከትምህርት ተቋማት የትምህርት ማስረጃ፣ዲፕሎማም ሆነ ዲግሪ አውጥተዋል
 • ብድር ተበደረዋል እንዲሁም ከፍለዋል
 • አክስዮን ገበተዋል የአክስዮን ድርሻ ተቀብለዋል
 • መብራት፣ውሃ ፣ የስልክ መስመር አስገብተዋል
 • ግብር ከፍለዋል

ከዚህ በላይ ያሉት ለአብነት ያክል የሚጠቀሱ ሲሆኑ  እኛ እርስዎ በፈለጉት መንገድ ያሰቡትን ጉዳይ የሚያሳካ  የውክልና ስልጣን እናዘጋጃለን። ዋናውና ትልቁ ሂደት ደግሞ የሚዘጋጀው የውክልና ስልጣን ይዘት ብቻ ሳይሆን ያ ውክልና  በኢትዮጵያም ሆነ በማንኛውም የአለም ክፍል  ተቀባይነት እንዲኖረው የሚደረገው   ሂደት ነው። ይህ ሂደት እርስዎ እንዳለወት የዜግነት እና የመኖሪያ ፈቃድ ሁኔታ  ሂደቱ የሚወስደው ጊዜ ሊያጥርም ሆነ ሊረዝም ይችላል ። ይህ ማለት ለምሳሌ  የአሜሪካ ዜግነት ያለው ኢትዮጵያዊና  ሰውና ቀኑ ያልተቃጠለ  የኢትዮጵያ ፓስፖርት ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ውክልናውን ለማጠናቀቅ የሚወስደው ጊዜ በጣም ይለያያል።
CHOOSE YOUR ORDER

 Amharic Power of Attorney or Wikilina

Amharic Power of Attorney or Wikilina